Fana: At a Speed of Life!

የስምንት ትምህርት ቤቶች ግንባታ ተጠናቆ ለርክክብና አገልግሎት ዝግጁ ሆኗል -የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት የተገነቡ አዲስ ስምንት ትምህርት ቤቶች ግንባታ ተጠናቆ ለርክክብና አገልግሎት ዝግጁ መሆናቸው ተገለጸ፡፡

የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት እንደገለጸው የተገነቡት ትምህር ቤቶች በተለያዩ ክልሎች እንደሚገኙ በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል፡፡

ትምህርት ቤቶቹ በአፋር ክልል ዱብቲ፣ በጋምቤላ አኝዋክ ዞን፣ በቤኒሻንጉል ክልል አሶሳ እና መተከል ዞን፣ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ዞን 02 እና 06 ቀበሌዎች፣ በአማራ ክልል ጎንደር ደባርቅ ከተማ እና ዋግኽምራ ዞን ሳህላ ሰለምት ወረዳ የተገነቡ መሆናቸውን ነው የገለጸው፡፡

የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ከዚህ ቀደም ግንባታቸው ተጠናቆ ለአገልግሎት የበቁ አምስት ትምህርት ቤቶችን ማስረከቡ ይታወሳል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.