Fana: At a Speed of Life!

የስትሮክ ህመም አስከፊነት

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአንጎል ውስጥ ደም መፍሰስ (ስትሮክ )ህመም አስከፊነት በአግባቡ ግንዛቤ በመያዝ ህብረተሰቡ ራሱን መጠበቅና መከላከል እንዳለበት ጤና ሚኒስቴር አሳሰቧል፡፡
 
ስትሮክ በአንጎላችን ክፍል ውስጥ ያለው የደም ዝውውር በተለያዩ ምክንያቶች በድንገት መቋረጥ ሲገጥመው የሚከሰት ህመም ነው።
የስትሮክ ህመም ራስን መግለጽ ያለመቻል፣ ግማሽ ጎን መጋረድና ግምሽ ጎን መስነፍ ሊያስከትል ይችላል።
 
በዓለም አቀፍ ደረጃም በዓመት በአማካይ ከአምስት ሚሊዮን በላይ ሰዎች በዚሁ ህመም ምክንያት ህይወታቸውን ያጣሉ።
 
በዓለም ላይ በስትሮክ በሽታ በአማካይ በየአራት ደቂቃው አንድ ሰው እንደሚሞትም ጥናቶች ያመለክታሉ።
 
በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከሚመዘገበው አጠቃላይ የሞት ምጣኔ ውስጥ 6 ነጥብ 23 በመቶው በስትሮክ ሳቢያ የሚከሰት እንደሆነ ተመልክቷል።
 
ጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ኒዩሮሎጂስቶች ማህበር ከፊታችን አርብ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በተለያዩ መርሃ ግብሮች
የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የስትሮክ ሳምንት በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።
 
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ እንደሉት ÷ በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ 13 ነጥብ 7 ሚሊየን ሰዎች በስትሮክ ሳቢያ ለህመም ይዳረጋሉ።
 
ጤና ሚኒስቴር ስትሮክን ለመከላከል የጤና ባለሙያዎችን በብዛት በማሰልጠን ለህብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲሰጡ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነም ተነግሯል፡፡
 
በሽታውን ለማከም የሚያገለግሉ መድሃኒቶችን እና አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች በየጤና ተቋማቱ ተደራሽ እየተደረጉ መሆኑንም ነው ዶክተር ደረጀ የገለጹት፡፡
የኢትዮጵያ ኒዩሮሎጂስቶች ማህበር ጸሐፊ ዶክተር ሜሮን አውራሪስ በበኩላቸው÷የዓለም የስትሮክ ቀን በአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ከፊታችን አርብ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ይከበራል ብለዋል፡፡
ህብረተሰቡ ከስትሮክ ራሱን ለመጠበቅ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣ የስብ መጠንን ማስተካከል እንደሚገባ መናገረቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.