Fana: At a Speed of Life!

የስዊዝ ቦይን ለአንድ ሳምንት ዘግታ የነበረችው መርከብ መንቀሳቀስ ጀመረች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ስዊዝ ቦይን ለአንድ ሳምንት ዘግታ የነበረችው ግዙፏ ዘ ኤቨር ጊቭን መርከብ መንቀሳቀስ መጀመሯ ተገለፀ።

400 ሜትር የምትረዝመው ግዙፍ እቃ ጫኚ መርከብን ከነበረችበት ሁኔታ 80 በመቶ መልኩ ተስተካክላ መንቀሳቀስ መጀመሯን ነው የስዊዝ ቦይ ባለስልጣናት ያስታወቁት።

ባለስልጣናቱ  መርከቧን ሙሉ በሙሉ ለማንቀሳቀስ በዛሬው ዕለት ተጨማሪ ስራዎች እንደሚከናወኑ ተናግረዋል፡፡

ዓለም ላይ ከፍተኛ የንግድ ልውውጥ የሚካሄድበት የስዊዝ ቦይ በኤቨር ጊቭን መርከብ ምክንያት ከተዘጋ አንድ ሳምንት ሆኖታል፡፡

በዚህም በየቀኑ 9 ቢሊየን ዶላር የሚገመት የሸቀጥ ግብይት ላይ መስተጓጎል ሲፈጥር ቆይቷል ብሏል ቢቢሲ በዘገባው።

በዚህ መተላለፊያ በየቀኑ ወደ ምዕራቡ ዓለም 5 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ዋጋ ያለው ሸቀጥ የሚንቀሳቀስ ሲሆን ወደ ምስራቁ ደግሞ 4 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር የሚገመት ሀብት ይዘዋወርበታል ተብሏል።

ዘ ኤቨር ጊቭን የተሰኘችው መርከብ የአራት እግር ኳስ መጫወቻ ሜዳዎች ርዝመት እንዳላትና በዓለም ላይ ግዙፍ ከሚባሉ ኮንቴነር ጫኝ መርኮች መካከል አንዷ መሆኗ ይነገራል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.