Fana: At a Speed of Life!

የሶማሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር አዲስ ካቢኔ አዋቀሩ

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 10 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሶማሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሃመድ ሁሴን ሮቤሌ ያዋቀሩትን አዲስ ካቢኔ ይፋ አድርገዋል።
አዲሱ ካቢኔ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ 26 ሚኒስትሮችን ያካተተ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ አራቱ ሴቶች መሆናቸው ተነግሯል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪም 17 ሚኒስትር ዲኤታዎችን እና የ26 ምክትል ሚኒስትሮችንም ዝርዝር ይፋ አድርገዋል።
ይፋ የተደረገው አዲሱ ካቢኔ በፓርላማው መጽደቅ ይኖርበታልም ነው የተባለው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሃመድ ሁሴን ሮቤሌ ባለፈው ሐምሌ 25 ቀን የሀገሪቱ ፓርላማ ከስልጣን ያባረራቸውን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀሰን አሊን መተካታቸው ይታወሳል።
ምንጭ፡-ቢቢሲ
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.