Fana: At a Speed of Life!

የሶማሊያ መሪዎች በተጓተተው የምርጫ ሂደት ላይ ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ (ፋርማጆ) እና የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሃመድ ሁሴን ሮብሊ ለረዥም ጊዜ የተጓተተውን የምርጫ ሂደት ለማስቀጠል ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገለፀ።
ሶማሊያ በዚህ ወር አዲስ ፕሬዚዳንቷን ለመምረጥ እቅድ ብትይዝም በሁለቱ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ሂደቱ ተጓቷል።
ፕሬዚዳንቱና ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሃገሪቱን የብሔራዊ መረጃ ደህንነት ኤጀንሲ ማን ይምራ በሚለው ሃሳብ ላይ ስምምነት አለመድረሳቸው ለምርጫው ሂደት መጓተት ምክንያት መሆኑ ይነገራል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ የኤጀንሲውን ኃላፊ ለመተካት የየራሳቸውን እጩዎች አቅርበው ነበር።
አሁን ላይ ስምምነት መድረሳቸው የተገለጸ ሲሆን፥ በፕሬዚዳንቱ የቀረቡት እጩ ኤጀንሲውን በጊዜያዊነት የሚመሩ ሲሆን የጠቅላይ ሚኒስትሩ እጩ ደግሞ በሚኒስትር ዲኤታ ማዕረግ ሌላ የስራ ድርሻ ይኖራቸዋል ተብሏል።
በጋራ በሰጡት መግለጫም ክልሎች በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ለታችኛው ምክር ቤት ምርጫ እንዲጀምሩ ጥሪ ማቅረባቸውን የአልጀዚራ ዘገባ ያመላክታል።
ሀገሪቱ በዚህ ወር አዲስ ፕሬዚዳንቷን ትመርጣለች ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ይህም የተወሳሰበውንና ቀጥተኛ ውክልና የለውም በሚል የሚተቸውን የሃገሪቱን ፓርላማ እንዲሁም የምርጫ ሂደት በአዲስ መልኩ ያሻሽላል ተብሎ ታምኖበታል።
በሚኪያስ አየለ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.