Fana: At a Speed of Life!

የሶማሊያ ብሔራዊ ጦር 40 የአልሸባብ አሸባሪዎችን ገደልኩ አለ

አዲስ አበባ፣ሰኔ 26፣2014(ኤፍ ቢሲ) የሶማሊያ ብሔራዊ ጦር 40 የአልሸባብ አሸባሪዎችን መግደሉን የሀገሪቱ የቴሌቪዥን ጣቢያ አስታወቀ፡፡
የአልሸባብ ታጣቂዎች በመካከለኛው ሶማሊያ ሸበሌ ግዛት በተደረገ ወታደራዊ ዘመቻ ስለመገደላቸው ነው የሀገሪቱን ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጠቅሶ ሲ ጅ ቲ ኤን የዘገበው፡፡
በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰው ፅንፈኛው አልሸባብ ቡድን ከአልቃይዳ የሽብር ኃይል ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚነገር ሲሆን፥ በሶማሊያ እና በአጎራባች አገሮች በርካታ የሽብር ጥቃቶች መፈጸሙንም ዘገባው አስታውሷል፡፡
የሶማሊያ ወታደራዊ ኃይሎች በአገሪቱ ሰሜን ምሥራቅ ክፍል ሀፉን ከተማ ውስጥ አፍቃሬ-አይሲስ ናቸው የተባሉ ሰባት ታጣቂዎችን ከአንድ ሳምንት በፊት መግደላቸው ይታወሳል።
የፑንትላንድ የፀጥታ ኃይሎች ሕገ ወጥ መሳሪያዎችን ለመሰብሰብ በአይ ኤስ የሽብር ቡድን የተላኩ ናቸው የተባሉ አራት ታጣቂዎችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውም ተገልጿል።
በተጨማሪም በሌላ አካባቢ ሌሎች ሦስት የአይ ኤስ ደጋፊዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፑንትላንድ ግዛት ወታደሮች በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
“ጀግኖች ወታደሮቻችን ይህንን የተሳካ ዘመቻ የፈጸሙት የአይ ኤስ ደጋፊ የሆነው አሸባሪ ቡድን” በተለያዩ አካባቢዎች የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመግታት ነው ብለዋል የግዛቷ ወታደሮች፡፡
የፑንትላንድ ወታደሮች የሽብር ቡድኑን ደጋፊዎች በቁጥጥር ስር ያዋሉት ከአካባቢው ማህበረሰብ ስለ ታጣቂው ቡድን እንቅስቃሴ ባገኙት መረጃ መሰረት መሆኑን ነው ያስታወቁት፡፡
በሶማሊያ የሚገኘው እና “የአይኤስ ክንፍ” እየተባለ የሚጠራው የሽብር ቡድን ዋና መሠረቱ በፑንትላንድ ግዛት ውስጥ ሲሆን፥ አልፎ አልፎ ከፑንትላንድ ጦር ጋር ውጊያ እንደሚደርግ ዥንዋ እና ሲጅቲኤን ዘግበዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.