Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌን ህዝብ ባህልና አብሮ የመኖር እሴት ከማሳደግ አንጻር ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሶማሌን ህዝብ ባህልና አብሮ የመኖር እሴት ከማሳደግ አንጻር ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የክልሉ ባህል ቱሪዝም ቢሮ  አስታወቀ።

የክልሉ ባህል  ቱሪዝም ቢሮ  ቢሮ ሃላፊ አቶ ኤልያሰ ሀብብ  እንደገለጹት የሶማሌ  ብሄረሰብ መገለጫ የሆነውን ቋንቋ፣ ባህልና ከለሎች ህዝቦች ጋር አብሮ የመኖር  እሴትን ከማሳድግና ከማጎልበት አንጻር በክልሉ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የተጀመረውን ሃገራዊ ብልፅግና ከግብ ለማድረስና ለውጡን ለማስቀጠል በሃገር ደረጃና  በክልል የተጀመረው ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን በመግለጽ ሃገራዊ ለውጡም  የሶማሌን ባህላዊ ቱውፊቶች በማጎልበትና የማህበረሰቡን  ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አንጻር ጉልህ ሚና እያበረከተ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

በክልሉ የሶማሌ ቋንቋ፣ ባህል፣ታሪክና ማንነት ለማሳደግና ለማበልጸግ የክልሉ መንግስት ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠትና የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ወደ ስራ በመግባት እንቅስቃሴ ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የሶማሌ ብሄረሰብ የራሱ የሆነ ቋንቋ፣ ባህል ፣ታሪክና ማንነት ያለው ህዝብ ነው ያሉት  ቢሮ ሃላፊው ይህን እሴቱን በመጠበቅና በማሳደግ ለቀሪው ትውልድ ከማስተላለፍ አንጻር የትምህርት ተቋማትና ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡

በ2012 በጀት አመት የተለያዩ ስራዎች መከናወናቸውን የገለጹት ቢሮ ሃላፊው ከተያዙ ፕሮጀክቶች ውስጥ በክልሉ እየተገነባ የሚገኘው የሶማሌ ባህል ማእክል ግንባታ አንዱ መሆኑን በመግለጽ ማእከሉም በጥሩ የስራ አፈጻጸም ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

በተለይም በ2013 በጀት አመት ከታቀዱ ፕሮጀክቶች ውስጥ በሶማሌ ብሄረሰብ ውስጥ የተለያዩ አኩሪ ታሪክና ገድል የፈጸሙ ግለሰቦችን ታሪክ በማጥናት ለህብረተሰቡ ተደራሽ የማድረግ ስራዎች እንደሚከናወኑ በመግለጽ በክልሉ የሶማሌ ማህበረሰብ  ማእከል ያደረጉ የጥናት ስራዎች በጀት በመመደብ  ስራዎች እንደሚከናወኑም  ገልጸዋል፡፡

ከሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች ጋር በጋራ በመሆንና የጋራ እሴቶችን በማጠናከር የተለያዩ የጥናት ስራዎችን ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ከፌዴራል ቅርስና ጥናት ጥበቃ ባለስልጣንና ከጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ በመሆን በክልሉ የሶማሌን ባህል፣ ታሪክና እሴት የሚያወሱ ሰፋፊ ጥናቶች እየተደረጉ መሆኑን ነው የተናገሩት።

የማንነት መገለጫ የሆኑትን ባህሎች፣ ቋንቋዎችና፣ ታሪኮች ባህላዊ እሴቶቻቸውን ሳይለቁ ተጠብቀው እንዲቆዩ የሚመለከታቸው አካለት የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ እንደሚገባም አመልክተዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

 

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.