Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ብልፅግናና የትግራይ ብልፅግና ፖርቲ በጅግጅጋ ከሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሶማሌ ብልፅግናና የትግራይ ብልፅግና ፖርቲ በጅግጅጋ ከሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ጋር በወቅታዊ ሐገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሒደዋል ።
በዛሬው ዕለት በጅግጅጋ የተደረገው የውይይት መድረክ በሶማሌ ብልፅግናና የትግራይ ብልፅግና ፖርቲዎች የተዘጋጀ ነው።
ከትግራይ ብልፅግና ከፍተኛ አመራርና የአስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ሙሉቀን ሐብቱ እና የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ወ/ሮ ሁሪያ አሊ ውይይቱን መርተዋል።
ለተወላጅ ተሳታፊዎቹ የህወሓት ጁንታ ከለውጡ ጀምሮ ሀገርን የማተራመስ ሴራና የህግ ማስከበር ሂደትና መልሶ የማልማት ተግባርን በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል ።
ተሳታፊዎችም ለወንድም የሶማሌ ህዝብ አብሮነት፣ ወዳጅና አቃፊነቱ አመስግነዋል።
የፅንፈኛው ቡድን የሰራው ክፉ ስራ ኢትዮጵያዊነትን የማይገልፅ፣ የትግራይን ህዝብን የማይወክል፣ የተወላጁንም አንገት ያስደፋ እንደሆነ መግለጻቸውን የክልሉ መንግስት ማስሚዲያ ዘግባል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.