Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል ለ2014 በጀት ዓመት ለስራ ፈጠራ 235 ሚሊየን ብር መድቧል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል በ2014 በጀት ዓመት ለሥራ ዕድል ፈጠራ 235 ሚሊየን ብር መመደቡን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ገለጹ፡፡
 
በጅግጅጋ ከተማ ለሁለት ወራት በክልሉ ስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን አዘጋጅነት በ85 ማህበራት መካከል ሲያካሄድ የነበረው ውድድር ተጠናቋል፡፡
 
ማህበራቱ ባቀረቡት ፕሮፖዛል እና የስራ ሀሳብ የተወዳደሩ ሲሆን÷ የተለያዩ ማጣሪያዎችን በማድረግ ነው ለፍፃሜ የደረሱት፡፡
 
በመርሃ ግብሩ ላይ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ከተለያዩ ማህበራ የተውጣጡ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡
 
አቶ ሙስጠፌ ከሙስናና ብልሹ አሠራር በፀዳ መልኩ በክልሉ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከናወነ የወጣቶች የስራ ፈጠራ መርሃ ግብር በመሆኑ የክልሉ መንግሥት ይህንን ተግባር ያበረታታል ብለዋል፡፡
 
የክልሉ መንግሥት ወጣቶችን በመንግሥታዊ የስራ መዋቅር ላይ ብቻ መቅጠር ሳይሆን ከፍተኛ በጀት በመመደብ የስራ እድል ፈጠራን ያጠናክራል ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ÷ ለዚህም በ2014 235 ሚሊየን ብር ተመድቧል ማለታቸውን የሶማሌ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡
 
የክልሉ የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ወይዘሮ ሂቦ አህመድ በበኩላቸው÷ ለሁለት ወራት የተለያዩ ማጣሪያዎች ተደርጎ 51 ማህበራት አሸናፊ መሆናቸውን ጠቁመው እንደዚህ ዓይት አሰራሮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስረድተዋል፡፡
 
በዛሬው ዕለትም ለመጨረሻው ዙር ለቀረቡ 51 አሸናፊ ማህበራት ሽልማት መበርከቱን የገለጹት ወ/ሮ ሂቦ÷ለአሸናፊ ማህበራቱም 35 ሚሊየን ብር የሚከፋፈል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.