Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል መንግስት በመላ ሀገሪቱ ሰላምና የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሶማሌ የሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በመላ ሀገሪቱ ሰላምና የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቀረበ።

የሶማሌ የሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ባወጨጣው ሳምንታዊ መግለጫ ነው ይህንን ያስታወቀው።

በመግለጫውም ከለውጡ ማግስት ጅምሮ የክልሉ መንግስት ለበርካታ ዓመታት ተደራርቦ የቆዩትን የዜጎች የሰላም፣ የመሰረተ ልማት፣ መልካም አስተዳደር፣ ዴሞክራሲ፣ የፍትህና ሰብዓዊ መብቶች ጥያቄዎችን በአግባቡ ለመመለስ በርካታ ጥረቶች ከማድረጉን አስታውሷል።

እንዲሁም በሁሉም የክልሉ አከባቢዎች የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ፕሮጀክቶች መስራቱን እንዲሁም በተያዘለት ጊዜ ገደብና በታቀደለት ጥራት ለማጠናቀቅ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ሲደረግለት መቆዩቱንም ገልጿል።

የሰላም ጉዳይ ለድርድር የማይቀርብ መሆኑን በመግለጫው ያነሳው የክልሉ መንግስት፥ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የሰላምና ህግን የማሰከበር ጉዳይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።

የትግራይ ህዝብ ከጁንታው አፈና ነፃ በመውጣቱ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ያስተላለፈ ሲሆን፥ የሶማሌ ክልል መንግስትና ህዝብ ሰብአዊ ድጋፍ ለማቅረብና ጁንታው ያወደማቸውን መሰረተ ልማቶች መልሶ በመገንባት ሂደት አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ አረጋግጧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.