Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል ምክር ቤት የሀብት ምዝገባ አዋጅ አጸደቀ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው የ5ኛ ዓመት 13ኛው መደበኛ ጉባኤ የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ አዋጅ ማጽደቁን የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን  ገለጸ።

የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ዳይሬክተር አቶ አብዱልከሪም አህመድ ÷ የክልሉ ምክር ቤት አባላት በቀረበላቸው የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት በማድረግ አፅድቀዋል፡፡

ምክር ቤቱ  የሀብት ምዝገባ አዋጁን ከማፅደቁም በተጨማሪ የክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅን በማሻሻል በክልሉ የተለያዩ መስሪያቤቶች ውስጥ የሚገኙ የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች ተጠሪነታቸው ለክልሉ የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን እንዲሆን መወሰኑንም አቶ አብዱልከሪም ገልፀዋል፡፡

የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ አዋጁ በክልሉ ምክር ቤት መጽደቁ ሙስናን ቀድሞ በመከላከልና የጥቅም ግጭትን ለመቀነስ እንደሚያግዝ ይታመናል።

ከዚህም በተጨማሪ ሀገራዊ የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ሥራዎችን ምሉዕ ለማድረግና ሀገራዊ መልክ ለማስያዝ የአዋጁ መፅደቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ከፌደራል የስነምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.