Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል ስራ አስፈፃሚ ካቢኔ የፊት ጭምብል ያልለበሰ ሰው አገልግሎት እንዳይሰጥ ወሰነ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሶማሌ ክልል ስራ አስፈፃሚ ካቢኔ ድርቅ ሊያመጣ የሚችለውን ጉዳት ለመቋቋም 22 ሚሊየን ብር በሙሉ ድምፅ አጸደቀ፡፡

ስራ አስፈጻሚ ካቢኔው ሊያጋጥም ስለሚችል ድርቅ እና የአካባቢው ሰላም ላይም ውይይት ማድረጉ ተገልጿል።

ከአደጋ ተጋላጭነት አያያዝ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ተነስተው ውይይት እንደተደረገባቸው የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሸን አስታውቋል።

በክልሉ የሰፈነው ሰላም ቀጣይነት እንዲኖረው ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዳለበትም አቅጣጫ ተቀምጧል።

በተጨማሪም በበጀት አመቱ እንዲሰራ የታቀደው የሶማሌ ክልል የባህል ማዕከል በአስቸኳይ ግንባታው እንዲጀመርም ውሳኔ ተላልፏል።

ከዚህ ባለፈም ኮቪድ 19 እንዳይስፋፋ ለመከላከል የፊት ጭምብል ያልለበሰ ማንኛውም ሰው አገልግሎት እንዳይሰጥ ተወስኗል ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.