Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል ነዋሪዎች የድጋፍ ሰልፍ አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) እውነተኛ ፌደራሊዝምን ለመተግበር እየሰራ ያለውን ብልፅግናን እንደግፋለን  በማለት የሶማሌ ክልል ነዋሪዎች በጅግጅጋ የድጋፍ ሰልፍ አካሄዱ።

በድጋፍ ሰልፉ ላይ ከተለያዩ 20 የከተማዋና አካባቢዋ ቀበሌዎች የተውጣጡ ከ20 ሺህ የሚበልጡ ነዋሪዎችም ተሳትፈዋል።

ነዋሪዎቹ በድጋፍ ሰልፉ ላይ ባለፉት ዓመታት የሶማሌ ህዝብ ሙሉ በሙሉ የዜግነት መብቱን ተነፍጎ መቆየቱን ተናግረዋል።

አሁን ላይ የብልፅግና ፓርቲ እውነተኛ ፌደራሊዝምን በመተግበር የክልሉ ህዝብ በሰላም በልማተ እና በፖለቲካ ተሳትፎ ተጠቃሚ መሆን መጀመሩን ነው ያነሱት።

ፓርቲው ያሳየውን መልካም ጅማሮ በማየትም ወደፊት አብረን እንሰራለን ብለዋል።

በሰልፉ ላይ የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

 

በፍሬህይወት ሰፊው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.