Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል የመጀመሪያው የጥናት ኮንፈረንስ  እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል የመጀመሪያው የጥናት ኮንፈረንስ በጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ ነው።

የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ እና የክልሉ መንግስት ያዘጋጁት ኮንፈረንሱ በዛሬው ዕለት ይጠናቀቃል።

የጥናት ኮንፈረንስ ላይ የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳደር  አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ፣ ከክልሉና ከተለያዩ የአለም ሀገራት ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የመጡ ምሁራን ተሳታፊ ሆነዋል።

ኮንፈረንሱ በኢትዮጵያ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በፓለቲካዊ፣ የማህበራዊና በዴሞክራሲ አስተዳደር ከተረጋገጡ ለውጦች አነፃር በሶማሌ ክልል ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት ያለመ መሆኑን ኤስ አር ቲቪ ዘግቧል።

ኮንፈረንሱ የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው በኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች  ውይይት እየተደረገባቸው ይገኛል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.