Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል ፀጥታ ቢሮ አመራሮች ከሶማሊያ ሪፐብሊክ የሂር ሼቤሌ ግዛት ሂራን ዞን አመራሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ፀጥታ ቢሮ አመራሮች ከሶማሊያ ሪፐብሊክ የሂር ሼቤሌ ግዛት ሂራን ዞን አመራሮች ጋር በፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በፌርፊር ወረዳ ተወያይተዋል፡፡

 
በውይይት መድረኩ የሶማሌ ክልል ሰላምና ደህንነት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሙባሽር ዱባድ፣ የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል ዋና አዛዥ ኮሚሽነር ጀነራል መሀመድ አህመድ፣ የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል መሀመድ አሊ ሀሰን እንዲሁም በሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ሂር ሻቤሌ ግዛት አመራሮችና ሌሎች የፀጥታ ተቋማት ተገኝተዋል።
 
በተጨማሪም በምክክሩ ላይ ከሶማሊያ በኩል የሂራን ዞን አሰተዳድር አቶ አሊ ጃይቴ ኡስማንና በሂራን ዞን የሚገኙት የሶማሊያ መከላከያ ሠራዊት 5ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ጄኔራል መሃሙድ ሀሰን፣ የሂር ሻቤሌ ግዛት የውሃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ሳላህ ሁሴን እና ሌሎች ባለስልጣናት ተሳታፊ ሆነዋል።
 
በሁለቱ ወገን በሰላም ዙሪያ በድንበር በኩል የአልሸባብና ሌሎች ፀረ ሰላም ሃይሎች ወደ ሁለቱም ድንበር ሰርገው እንዳይገቡ፣ ግጭቶችን በጋራ ለመከላከል እና በድርቅ የተጎዱትን ዜጎች ለመርዳት በቅንጅትና በትብብር አብሮ ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱን ከሶማሌ ክልል የጸጥታ ቢሮ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.