Fana: At a Speed of Life!

የሶስቱ ሀገራት የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ዛሬ ሊያካሂዱት የነበረው ስብሰባ ሱዳን ባለመገኘቷ ሳይካሄድ ቀርቷል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ዛሬ በህዳሴ ግድብ ጉዳይ ዙሪያ ሊያካሂዱት ታስቦ የነበረው የበይነ-መረብ ስብሰባ ሱዳን ባለመገኘቷ ሳይካሄድ መቅረቱን የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የዕለቱ ሰብሳቢ የሆነችው ኢትዮጵያ ባስተላለፈችው ጥሪ መሰረት የግብጽ ልዑክ እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት ባለሙያዎች እና ታዛቢዎች ተገኝተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት የሰየማቸው ባለሙያዎች ባዘጋጁት ሰነድ ላይ ያሏትን የልዩነት ሃሳቦች ለአፍሪካ ህብረት የአስፈጻሚ ምክርቤት ሊቀመንበር በማሳወቅ ሰነዱን ለሶስትዮሽ ድርድር እንደግብዓት ለመጠቀም መስማማቷ ይታወሳል፡፡

ሆኖም የልዩነት እና አንድነት ሃሳቦችን ለማጠናቀር የታሰበው የዛሬው ስብሰባ በሱዳን አለመገኘት ምክንያት ሳይካሄድ ቀርቷል፡፡

ይኸው ለአፍሪካ ህብረት አስፈጻሚ ምክርቤት ሊቀመንበር በኢትዮጵያ በኩል መገለጹን ሚኒስቴሩ ያወጣው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳ
የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.