Fana: At a Speed of Life!

የሶስቱ የብሄራዊ ፀጥታ ተቋማት ዩኒቨርሲቲዎች በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ፣ የኢትዮጵያ ፓሊስ ዩኒቨርሲቲና የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በጋራ መስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሜጀር ጄኔራል ደሳለኝ ተሾመ፣ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ኮሚሽነር መስፍን አበበ እና የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ፕሬዝዳንት ወንድወሰን ካሳ ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ ተቋማቱ በትምህርት፣ ሥልጠና፣ ጥናትና ምርምር እንዲሁም በማህበረሰብ አገልግሎት ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸው እንደሆነ ተገልጿል።

የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሜጀር ጄኔራል ደሳለኝ ተሾመ እንደተናገሩት፤ ስምምነቱ ተቋማቱ የጋራ ተልዕኳቸውን በትብብር እንዲወጡ ያስችላል።

ኢትዮጵያ ያለችበት ወቅታዊ ሁኔታ በትብብር መስራትን በእጅጉ የሚጠይቅ መሆኑን ገልጸው÷ “በትምህርት፣ ሥልጠና ጥናትና ምርምር በትብብር በመስራት የጋራ ተልዕኳችንን ማሳካት አለብን” ሲሉ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ኮሚሽነር መስፍን አበበ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ የወጠነቻቸው ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ከግብ እንዲደርሱ የተቋማቱ ሚና የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።

ተቋማቱን በሰው ሃይል በማጠናከር ሰላምና ደህንነት በፅኑ መሰረት ላይ ማቆም እንደሚገባ ጠቅሰዋል።

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ፕሬዚዳንት አቶ ወንድወሰን ካሳ እንዳሉት÷ የተቋማቱ የሥራ ባህርይ ተመሳሳይ በመሆኑ ከትምህርታዊ ትብብር ባሻገር በማህበረሰብ አገልግሎት ዙሪያ በጋራ መስራታቸው አስተዋፅኦቸውን የላቀ ያደርገዋል።

ከሶስቱ ተቋማት የተውጣጣ የቴክኒክ ኮሚቴ “ስምምነቱ ተግባራዊ እንዲሆን ይሰራሉ” ሲሉም ተናግረዋል።

በዚሁ ወቅትም የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ያሳተመው የህግ ማስከበር መጽሐፍ መመረቁን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.