Fana: At a Speed of Life!

የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያስገነባቸውን ትምህርት ቤቶች አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን ያስገነባቸውን ሁለት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አስመረቀ፡፡

በምረቃው ስነ ስርአት ላይ ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያችውን ጨምሮ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን፣ የክልሉ ምክትል አፈ ጉባኤ እና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል::

ትምህርት ቤቶቹ በ13 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነቡ ናቸው፡፡

በውስጣቸውም የአስተዳደር ህንጻ፣ የመማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ ሙከራ፣ ቤተ መጽሐፍት፣ የስብሰባ አዳራሽ እና የመጸዳጃ ህንጻዎችን አካተዋል፡፡

ትምህርት ቤቱ በሙሉ አቅሙ መቀበል ሲጀምር በሁለት ፈረቃ 1 ሺህ 600 ተማሪዎችን የመቀበል አቅም እንዳለው ተነግሯል፡፡

በትምህርት ቤት ርቀትና እጥረት ምክንያት ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ገበታ ላልላኩ የአሶሳ ወረዳ ነባ ኮምሽጋ እንዲሁም አዋሳኝ ቀበሌ ነዋሪዎች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት በመላክ እድሉን እንዲጠቀሙ ጽህፈት ቤቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ጽህፈት ቤቱ በዛሬው እለት ያስመረቃችውን ጨምሮ እንደ ሃገር ግንባታችው ተጠናቆ ያስመረቃቸው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 10 የደረሱ ሲሆን ቀሪዎቹን በቅርብ ቀን እንደሚያስመርቅ ተገልጿል፡፡

ትምህርት ተደራሽ ባልሆነባቸው ሌሎች አካባቢዎች የትምህርት ቤት ግንባታው በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚጀመርም አስታውቋል፡፡

በተመሳሳይ ጽህፈት ቤቱ በጋምቤላ ክልል ጋምቤላ ከተማ ያስገነባውን ትምህርት ቤት ዛሬ ያስመርቃል፡፡

በፍሬህይወት ሰፊው

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.