Fana: At a Speed of Life!

የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በአዲስ አበባ ለሚገኙ አካል ጉዳተኞች የዊልቸር ድጋፍ አበረከተ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በአዲስ አበባ ለሚገኙ አካል ጉዳተኞች የዊልቸር ድጋፍ አበረከተ፡፡
ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ዛሬ ከአዲስ አበባ ከተማ ለተውጣጡ 72 አካል ጉዳተኞች የመንቀሳቀሻ ዊልቸሮችን በስጦታ አበርክተዋል፡፡
ስጦታ ባበረከቱበት ወቅት እንዳሉትም ይህ ስራ በቀጣይነት በአዲስ አበባ እና በክልሎች ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
የዊልቸር ስጦታዎቹ የተገኙት ሞቢሊቲ ወርል ዋይድ እና የአብ ሜዲካል ከተባሉ በጎ አድራጊ ድርጅቶች መሆኑ ታውቋል፡፡
ዊልቸሮቹ በተለይም በተለያየ የግል ስራ ላይ በመሰማራት ተንቀሳቅሰው ገቢ ለማግኘት ለሚጥሩ የአካል ጉዳተኞች ተስማሚ ሆኖ የተሰሩ በመሆናቸው ለስራ ፈጠራ ከፍተኛ እገዛ ይኖራቸዋል መባሉን ከፅህፈት ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.