Fana: At a Speed of Life!

የቀድሞዉ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ሳርኮዚ በሙስና ወንጀል እስር ተፈረደባቸው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኒኮላስ ሳርኮዚ በሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ተብለው የአንድ ዓመት እስር ተፈረደባቸው፡፡

የ66 ዓመቱ ሳርኮዚ ከፈረንጆቹ 2007 እስከ 2012 ድረስ ፈረንሳይን መርተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ለእስር የተዳረጉት ከምርጫ ዘመቻቸው ጋር በተያያዘ ለቀረበባቸው ክስ ጉዳዩን ከያዙት ዳኛ ጋር ተገቢ ያልሆነ ግንኙነት ነበራቸው በሚል ነው ተብሏል፡፡

ለዳኛ አዚበርት በሞናኮ ትልቅ ስልጣን ለመስጠት መሞከራቸውም ነው የተገለጸው፡፡

ሆኖም ፕሬዚዳንቱ አንዳችም የሙስና ወንጀል አልፈጸምኩም ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ድርጊቱን ፈጸሙ የተባለው በ2007 የምረጡኝ ዘመቻ ወቅት ነው፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም የሶስት አመት የእስር ቅጣት የተወሰነባቸው ሲሆን፥ አንድ አመቱን በእስር ቅጣት የሚያሳልፉ ይሆናል፡፡

ሁለት አመቱ የእስር ቅጣት ደግሞ ወንጀል ፈጽመው ከተገኙ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

በፈረንሳይ ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ የእስር ቅጣት የተፈረደባቸው ሁለተኛው ርዕሰብሄር መሆናቸውን ከፍራንስ 24 ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.