Fana: At a Speed of Life!

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ ከኬንያው ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የግሪን ሪቮሉሺን አፍሪካ ጥምረት ሊቀመንበር ሀይለማሪያም ደሳለኝ የተመራ ልዑክ ከኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር ተወያይተዋል።

የልዑክ ቡድኑ የግሪን ሪቮሉሺን አፍሪካ ጥምረት ፕሬዚዳንት የሆኑትን ዶክተር አግነስ ካሊባታን ያካተተ መሆኑ ተመላክቷል።

በዚህም ውይይት በመጪው መስከረም ወር በኬንያ ናይሮቢ ስለሚካሄደው የግሪን ሪቮሉሺን አፍሪካ ጥምረት ስብሰባ ዙሪያ ለፕሬዚዳንት ኡሁሩ ገለጻ ተደርጓል።

የልዑካን ቡድኑ ኬንያ የጥምረቱን ስብሰባ አስተናጋጅ የሆነችው በሥነ ምግብ እና የምግብ ዋስትና ላይ በሰራችው ስራ መሆኑን ገልጿል።

ይህ ስብሰባ የሀገሪቱን ስኬት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማሳወቅ አጋዥ መሆኑንም ለፕሬዚዳንት ኡሁሩ ገለጻ መደረጉን ከኬንያ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.