Fana: At a Speed of Life!

የቀድሞ ፍቅረኛውን በሽጉጥ ተኩሶ የገደለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 28፣2013(ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞ ፍቅረኛውን በሽጉጥ ተኩሶ በመግደል የተሰወረውን ግለሰብ በሰዓታት ልዩነት ውስጥ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ገርጂ ጌች ግሮሰሪ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው ተብሏል፡፡
በግሮሰሪው ውስጥ በመስተንግዶ ስራ ተቀጥራ የምትሰራው ከ18 እስከ 19 ዓመት የሚገመት ዕድሜ ያላት እንዬ ጀግኔ የተባለችው ወጣት እና የባጃጅ አሽከርካሪ የሆነው ሙሉጌታ መለሰ ለ6 ወራት ያህል በፍቅር ጓደኝነት አብረው ስለመቆየታቸው መረጃ ማግኘቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል፡፡
ነገር ግን እንዬ ጀግኔ በመካከላቸው በተፈጠረ አለመግባባት በፍቅር ጓደኝነቱ አብራ መዝለቅ ባለመፈለጓ ይህንኑ ነግራው ግንኙነታቸው መቋረጡ ተገልጿል።
ሆኖም ተጠርጣሪው ሙሉጌታ መለሰ እሷን ለመግደል አስቦ በ10 ሺህ ብር ሽጉጥ እንደገዛ እና ታህሳስ 27 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ 3 ሰዓት ገደማ የቀድሞ ፍቅረኛው እንዬ ጀግኔ ከስራ ወጥታ ወደ ቤቷ እየሄደች በነበረበት አጋጣሚ ጠብቆ በሽጉጥ ተኩሶ አፍንጫዋ አካባቢ በመምታት ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጉን ፖሊስ ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
ተጠርጣሪው ሙሉጌታ መለሰ ወንጀሉን ፈፅሞ ቢሰወርም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መረጃው ከደረሰው በኋላ ባደረገው ብርቱ ክትትል 24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ወንጀሉን ከፈፀመበት ሽጉጥ ጋር በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጠራ እንደሚገኝ ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.