Fana: At a Speed of Life!

የቄለም ወለጋ ዞን አባገዳዎች እና ሀደ ሲንቄዎች ለሸፈቱ ታጣቂዎች የሠላም ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቄለም ወለጋ ዞን የሚገኙ አባገዳዎች እና ሀደ ሲንቄዎች ለሸፈቱ እና ጫካ ለገቡ ታጣቂዎች ለመንግስት እጅ እንዲሰጡ እና በሠላም ወደ ኅብረተሰባቸው እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቀረቡ፡፡

የዞኑ አባገዳዎች እና ሀደ ሲንቄዎች “ለሀገራችን የሰላም ጊዜ ነው ፤ መሳሪያ ታጥቆ ጫካ መግባት፣ ደም ማፍሰስና ንብረት ማውደም አያስፈልግም” ብለዋል በጥሪያቸው።

“ማንኛውም ለኅብረተሰቡ እታገላለሁ የሚል አካልም ሀሳቡን በነጻነት በሰላማዊ መንገድ መግለጽ አለበት እንጂ ጫካ መግባት አያስፈልግም” ሲሉም በጥሪያቸው መምከራቸውን ከቄለም ወለጋ ዞን ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.