Fana: At a Speed of Life!

የቅራቅርንና የማይጸብሪን የጦር ግምባር በመምራት ድል ያደረጉት የኮሌኔል አለምነው ሞላ የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈጸመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የቅራቅርንና የማይጸብሪን የጦር ግምባር በመምራት ድል ያደረጉት የ33ኛ ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ ኮሎኔል አለምነው ሞላ የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈጸመ።

በህይወት ታሪካቸው እንደተገለጸው የማይጸብሪን ግንባር በመምራትና አካባቢውን ከጁንታው ነፃ በማድረግ የሕግ ማስከበር ዘመቻው እንዲሳካ ሀላፊነታቸውን በጀግንነት የተወጡ የጦር መሪ ናቸው።

የውትድርና ህይወትን በ17 ዓመታቸው የጀመሩትና ለ36 ዓመታት በትግል የቆዩት ኮሎኔል አለምነው በ51 ዓመታቸው በሀገረ ሠላም የጁንታውን ቡድን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከጠላት ጋር በተካሄደ ውጊያ ነው ህይወታቸው ያለፈው።

የቀብር ሥነ ሥርዓታቸውም በጀግንነት ባህልና በክብር በደቡብ ጎንደር ዞን በንፋስ መውጫ ከተማ በቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን ጥር 03 ቀን 2013 ዓ.ም ተፈጽሟል።

የ5 ልጆች አባት የሆኑት ኮሎኔል አለምነው ደርግን በማስወገድ፣ በኢትዮ ኤርትራና በሠላም አስከባሪነት ዘመቻዎችና በተለያዩ የትግል ቦታዎች ጀግንነታቸውን ያሳዩ ፅኑ የጦር መሪ እንደነበሩ አብመድ ዘግቧል ።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.