Fana: At a Speed of Life!

የቆዳ ኢንዱስትሪ ዘርፉን ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገለፀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ 7 ወራት የወጪ ንግድ አፈጻጸም 1.8 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የግብርና ምርት ዘርፍ 1.178 ቢሊዮን ፣የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ 211.4 ሚሊዮን፣ የማዕድን ዘርፍ 373.7 ሚሊዮን እና ሌሎች ዘርፎች 50.6 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ በማስገኘት ቀዳሚውን ድርሻ መያዛቸውን ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

የወጪ ንግድ ገቢው በበጀት ዓመቱ ከታቀደው 88% ያሳካ ሲሆን ከአምናው በጀት ዓመት ተመሳሳይ 7 ወራት ከተገኘው 1.57 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ጋር ሲነጻጸር የ15% ዕድገት ማሳየቱን ሚኒስቴሩ ገልጿል ፡፡

የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ከባለፈው በጀት ዓመት አፈፃፀም ጋር ሲነፃፀር ያስገኘው የወጪ ንግድ ገቢ ዝቅተኛ በመሆኑ ዘርፉ ለስራ ዕድል ፈጠራና ለሀገር የኢኮኖሚ ዕድገት ከሚጫወተው ሚና አንጻር ችግሮችን በመፍታት የዘርፉን ሀገራዊ የኢኮኖሚ አበርክቶ ለማሻሻል እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡

ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ የቆዳና ቆዳ ውጤቶች አምራቾችና ላኪዎችን በመለየት የውጭ ምንዛሬ እንዲያገኙ፣ ከኖራ ፋብሪካዎች ተጨማሪ ምርት እንዲቀርብ፣ ጨው አቅራቢ ድርጅቶች በሚፈለገው መጠን እንዲያቀርቡ በማድረግ ፣በቆዳ አቅራቢዎች መጋዘን የሚገኘውን ጥሬ ቆዳና ሌጦ ከፋብሪካዎች ጋር በማስተሳሰር እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመስራት ዘርፉ አሁን ካለበት ችግር ተላቆ በገቢ ተወዳዳሪ እንዲሆንና ለስራ ዕድል ፈጠራና ለሀገር ዕድገት የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ ለማሳደግ ሁሉም የሚመለከተው አካል ርብርብ ማድረግ እንዳለበት ተመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.