Fana: At a Speed of Life!

የበለጸጉ ሀገራት የዝንጀሮ ፈንጣጣ ክትባት በቅድሚያ ለማግኘት ሽሚያ ላይ ናቸው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢኮኖሚ የበለጸጉ ሀገራት አፍሪካን በመዘንጋት የዝንጀሮ ፈንጣጣ ክትባትን በቅድሚያ በእጃቸው ለማስገባት ሽሚያ ላይ መናቸው ተገልጿል፡፡

የበለጸጉ ሀገራት በሚሊየን የሚቆጠር የዝንጀሮ ፈንጣጣ ክትባት ለመግዛት እየጠየቁ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

ሀገራቱ አፍሪካን በመዘንጋት ክትባቱን በእጃቸው ለማስገባት የሚያደርጉት ሽሚያ በአኅጉሪቱ የቫይረሱ ሥርጭት እንዲባባስ እና ሚሊየኖች አደጋ ላይ እንዲወድቁ የሚገፋ አዝማሚያ መሆኑም ነው የተነገረው፡፡

በአሁኑ ጊዜ ቫይረሱ ወደ ሰው የመተላለፊያ አዝማሚያው አስጊ በሚባል ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የኅብረተሰብ ጤና ባለሥልጣናት አስታውቀዋል፡፡

አሁን ላይ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት በበለጸጉት ሀገራት የታየው አፍሪካን አግልሎ ክትባቱን በቅድሚያ የማግኘት ኢ-ፍትሃዊ አዝማሚያና ፍላጎት ሊደገም ይችላል የሚል ሥጋት በአንዳንድ ተቺዎች እየተንጸባረቀ እንደሚገኝም የሲጂቲ ኤን ዘገባ ይጠቁማል ፡፡

በአሜሪካ ጆርጂያ በሚገኘው ኤሞሪ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ረዳት የሕክምና ፕሮፌሰር የሆኑት ዶክተር ቦጉማ ካቢሰን ቲታንጂ ÷ የበለጸጉ ሀገራት የዝንጀሮ ፈንጣጣን ለመቆጣጠር በሚሊየን የሚቆጠር ክትባት ለመግዛት ሲሰለፉ ይታያሉ፤ አንዳቸውም ግን ከራሳቸው አልፈው ገዳዩ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ እየተሰራጨ ለሚገኝባት አፍሪካ የማካፈል ዕቅድ እንዳላቸው አላሳወቁም ብለዋል፡፡

የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል ÷ የቫይረሱ ሥርጭት አኅጉሪቱን እንደሚያሰጋት ያስታወቀ ሲሆን፥ ክትባቱ በቅድሚያ እንዲሰጣትም ጥያቄ አቅርቧል፡፡

የማዕከሉ ተጠባባቂ ዳይሬክተር አህመድ ኦግዌል ” ወረርሽኙ ለአፍሪካ ሥጋት ከሆነ የተቀረው ዓለምም ሥጋት ላይ ነው” ሲሉ ነው ሁኔታውን የገለጹት።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.