Fana: At a Speed of Life!

የበረሀ አንበጣ ወረርሽኝ በአማራ፣ ትግራይ እና አፋር ክልሎች አዋሳኝ ቦታ ላይ መከሰቱን የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የበረሀ አንበጣ ወረርሽኝ በአማራ፣ ትግራይ እና አፋር ክልሎች አዋሳኝ ቦታ ላይ መከሰቱን የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ።
 
ሚኒስትር ዲኤታው ዶክተር ማንደፍሮ ንጉሴ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የበረሀ አንበጣው በመኸር ከተሸፈነው ሰብል ላይ በተለያዩ ክልሎች በ88 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ተከስቶ እንደነበር ተናግረዋል፡፡
 
አሁን ላይም 70 በመቶ የሚሆነውን መከላከል መቻሉንም ነው የተናገሩት።
በሶስቱ ክልሎች ላይ የሚገኘውን የአንበጣ መንጋ በኬሚካል ርጭት እና በባህላዊ መንገድ ለመቆጣጠር እየተሰራ ነው ተብሏል።
 
ለዚህም በስድስት አውሮፕላኖች እና በ81 ተሽከርካሪዎች የኬሚካል ርጭት እየተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
 
ህብረተሰቡም የመከላከል ስራውን ውጤታማ ለማድረግ እና በመኸር ሰብል ላይ የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ መንጋው የሚታይባቸውን ቦታዎች በፍጥነት ለሚኒስቴሩ እንዲያሳውቅም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
 
ከበረሀ አንበጣ መንጋው በተጨማሪም በአገዳ ሰብሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርሰው ተምችም በትግራይ ክልል መከሰቱን ጠቅሰዋል፡፡
 
ከዚህ አንጻርም ሁለቱንም ለመከላከል ሰፊ ስራን እንደሚጠይቅ እና መረባረብ እንደሚገባም አንስተዋል፡፡
 
በዙፋን ካሳሁን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.