Fana: At a Speed of Life!

የበርሃ አንበጣ መንጋን በዘላቂነት መካላከል እንዲቻል ለኢትዮጵያ እገዛ የሚያደርጉ የእስራኤል ባለሙያዎች ነገ አዲስ አበባ ይገባሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የበርሃ አንበጣ መንጋን በዘላቂነት መካከክል በሚቻልበት ዙሪያ ለኢትዮጵያ እገዛ የሚያደርጉ የእስራኤል ባለሙያዎች ቡድን ነገ አዲስ አበባ እንደሚገባ የእስራኤል ምክትል የደህንነት ሚኒስትር ተናገሩ።
ምክትል ሚኒስትር ጋዲ ይባርከን በየጊዜው እየተከሰተ በሰብል ላይ ከባድ ውድመት የሚያስከትለውን የበርሃ አንበጣ መንጋ ዙርያ የእሳት ማጥፋት አይነት ስራ ከማከናወን ባለፈ ዘላቂ መፍትሄ ያሻዋል ነው ያሉት።
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ ይህን ለማድረግ ደግሞ በበርሃ አንበጣ መከላከል ስራ ላይ ተጠምደው የሚገኙ ባለሙያዎችን ክህሎት ማሳደግ ይገባል ብለዋል።
ይህን ስራ ለማከናወንም ነገ የእስራኤል ባለሙያዎች ወደ አዲስ አበባ ይገባሉ ሲሉ ነው የተናገሩት።
በዚህም የበርሃ አንበጣ በየጊዜው ሲከሰት እንዴት በፍጥነት ውድመት ሳያደርስ መከላከል በሚቻልብት ዙርያ ስልጠና እና ድጋፍ ይሰጣሉ ነው ያሉት።
ምክትል ሚኒስትሩ እስራኤል ለኢትዮጵያ በመስኖ ልማት ዙሪያ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቅጥል ተናግርዋል።
በባህሩ ይድነቃቸው እና በስላባት ማናዬ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.