Fana: At a Speed of Life!

የ’በቃ’ ዘመቻ አካል የሆነ ሰልፍ በሜልቦርን ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የ’በቃ’ ወይም ‘#NoMore’ ዘመቻ አካል የሆነ ሰላማዊ ሰልፍ በአውስትራሊያ ሜልቦርን ከተማ በበሀገሪቱ ፓርላማ ፊት ለፊት ተካሂዷል።
ሰልፈኞቹ ባሰሙት መፈክር የምዕራቡ ዓለም አንዳንድ አገራት በኢትዮጵያ ላይ እያደረጉት ያለውን ያልተገባ ጫናና ጣልቃ ገብነት አውግዘዋል።
የምዕራባውያኑ መገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ ላይ የሚያሰራጯቸውን ሀሰተኛ ዘገባዎች እንዲያቆሙና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አሸባሪው ሕወሓት በአማራና አፋር ክልሎች የፈጸማቸውን በደሎች እንዲያወግዙ ጠይቀዋል።
አሸባሪው የሕወሓት ቡድን ድርጊቶች በዓለም አቀፍ ወንጀል የሚያስጠይቅ እንደሆም አስገንዝበዋል።
‘ኢትዮጵያ አትፈርስም፣ ኢትዮጵያ ታሸንፋለች፣ ከኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት ጎን ነን፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በሕዝብ ድምጽ የተመረጠውን መንግስት ማክበርና እውቅና መስጠት አለበት’ የሚሉና ሌሎች ‘የበቃ’ እንቅስቃሴ መልዕክቶች በሰልፉ ላይ ተላልፈዋል።
በሰላማዊ ሰልፉ ላይ በአውስትራሊያ የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ አባላትና የኢትዮጵያ ወዳጆች መሳተፋቸውን ኢዜአ ከሰልፉ አዘጋጆች ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ሰልፉን ያዘጋጁት በአውስትራሊያ የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ አባላት መሆናቸው ተገልጿል።
‘የበቃ’ ወይም ‘#NoMore’ ዘመቻ አካል የሆኑ ሰላማዊ ሰልፎች ዛሬ በዴንማርክ ኮፐንሀገንና በግሪክ አቴንስ ይካሄዳሉ።
‘የበቃ’ ወይም #NoMore እንቅስቃሴ አፍሪካ፣ አውሮፓ፣ እስያ፣ ሰሜን አሜሪካና ኦሺኒያ አህጉራትን አዳርሷል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.