Fana: At a Speed of Life!

የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራምን በጋራ ለማስፈፀም የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ፊርማ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 11፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራምን በጋራ ለማስፈፀም የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ፊርማ ተካሄደ።

የሰላም ሚኒስቴር ብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራምን በጋራ ለማስፈፀም ከክልሎችና ከከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮዎችና ከዩኒቨርስቲዎች ጋር የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ፊርማ ስነ ስርዓት ተካሂዷል።

በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ የሰላም ሚኒስትር  ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም

ወጣቶች መሰረታዊ የሆኑ የሰላም እሴቶችን አዉቀዉ ወደ ተግባር እንዲያዉሉ ታስቦ የተቀረፀ ፕሮግራም ነዉ ብለዋል።

ሚኒስትሯ  ፕሮግራሙ ኢትዮጵያ ሀራቸውን የሚወዱና የአገልጋይነት ስሜት የተላበሱ ወጣቶችን ለማፍራት ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርካቶ በበኩላቸዉ ኢትዮጵያ የወጣቶች ሀገር መሆኗን ገልፀዉ ይህ ፕሮግራም ወጣቶች በትምህርት ያገኙትን እዉቀት ወደ ተግባር ለመቀየር ትልቅ ፋይዳ አለዉ ብለዋል።

ዶክተር ሳሙኤል የሰላም ሚኒስቴር ይህን ሀላፊነት ወስዶ በመንቀሳቀሱ አመሰግነዉ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን ለማገዝ ዝግጁ እንደሆኑ መናገራቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም ሁለት ዙር ያለዉ ሲሆን በመጀመሪያው ዙር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተመረቁ ወጣቶችን የሚያካት ሲሆን በሁለተኛዉ ዙር ደግሞ ከቴክኒክና ሙያ ተቋማት የተመረቁ ወጣቶችንና ትምህርት ያቋረጡ ወጣቶችን ያካትታል ተብሏል::

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.