Fana: At a Speed of Life!

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 444 ተማሪዎችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ሲያስተምራቸው የነበሩ 2 ሺህ 444 ተማሪዎችን አስመረቀ፡፡

ተመራቂዎቹ በ2012 ዓ.ም መመረቅ የነበረባቸው ሲሆን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ትምህርት በመቋረጡ የምረቃ ፕሮግራማቸው ዛሬ ተካሂዷል፡፡

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ጫላ ዋታ ትምህርታቸው በወረርሽኙ ምክንያት ተቋርጦ የነበረ ቢሆንም ማካካሻ ወስደው ዛሬ ለምርቃት መብቃታቸውን አንስተዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በ2013 የትምህርት አመት የኮቪድ-19 ፕሮቶኮልን ተግባራዊ በማድረግ ከ6 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅት ማድረጉን አስረድተዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከተመሰረተበት 2004 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ስድስት ዓመታት 8 ሺህ ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን፤ ባሳለፍነው ዓመት ከ17 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ እያሰለጠነ ይገኛል፡፡

በዚህም በቅድመ ምረቃ፣ ድህረ-ምረቃ እና ፒኤችዲ ፕሮግራም ስልጠና የሚሰጥ ሲሆን፣ በፒኤችዲ ፕሮግራም የገዳ ስርዓት ትምህርትን ይሰጣል፡፡

ተመራቂ ተማሪዎቹ በ8 ኮሌጆች በሚገኙ 35 የትምህርት መስኮች የሰልጠኑ ናቸው፡፡

ብዙአለም ቤኛ እና ሀቢብ ሞሃመድ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.