Fana: At a Speed of Life!

የቡድን 20 ሃገራት የብድር ማመጣጠኛ የውሳኔ ሃሳብ ወቅታዊና ጠቃሚ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የገንዘብ ሚኒስቴር በቡድን 20 አባል ሃገራት አበዳሪዎች ኮሚቴ የተቀመጠዉ የብድር ማመጣጠኛ የውሳኔ ሃሳብ ወቅታዊና ጠቃሚ መሆኑን አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ÷ የአበዳሪ ኮሚቴዉ ቡድን ዛሬ ይፋ ያደረገዉ የብድር ማመጣጠን ስተራቴጂ ለኢኮኖሚው ፍላጎቶች ተስማሚ የሆነ ብድር ለማቅረብ እና የአገሪቱን ማክሮ- ኢኮኖሚ ለማረጋጋት ጠቃሚ እርምጃ መሆኑን አስረድቷል፡፡
በኮሚቴው ዉሳኔም ደስተኛ መሆኑን ገልጿል፡፡
የብድር ኮሚቴው ያሳየውን ቁርጠኝነት ያደነቀው ሚኒስቴሩ ፥ ውሳኔው የአበዳሪ አገራትን የብድር አፈጻጸም የጋራ ማዕቀፍ መሰረት ያደረገና ኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚዋን ለማረጋጋት የምታደርገውን መሰረታዊ እርምጃ እንደሚደግፍ አስታውቋል።
በተለይም የኮሚቴው የጋራ ሰብሳቢዎች የሆኑት ፈረንሳይና ቻይና የአበዳሪዎች ኮሚቴ እንዲቋቋም ላደረጉት ያላሰለሰ ጥረትና የኢትዮጵያ መንግስት በወቅቱ ጥያቄውን እንዲያቀርብ ዕድል በመስጠት ጭምር እስካሁን ላሳዩት ድጋፍ ሚኒስቴሩ ምስጋና አቅርቧል።
ይህ የብድር ማመጣጠኛ ስትራቴጂ በኮቪድ 19 ለተጎዳው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሚናዉ ከፍተኛ መሆኑንም ሚኒስቴሩ አሰታዉቋል፡፡
ሚኒስቴሩ አሁን ላይ የሃገር በቀል የአኮኖሚ ዕቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ እና የተረጋጋ ኢኮኖሚ ለመፍጠር እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡
የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይ ኤም ኤፍ ለኢትዮጵያ ባደረገዉ የረጅም ጊዜ ብድር እና ለተደረጉት የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች እዉቅና መስጠቱንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የአበዳሪ ሀገራት የጋራ ማዕቀፍ የቡድን 20 ሀገራትንና የፓሪስ ክለብ የሚባሉትን አበዳሪዎች በማቀናጀትና በማስተባበር የታዳጊ አገሮችን ዕዳ እንደየአገሩ ሁኔታ ለማጤን የሚያስችል ስርዓት እንደሚከተል ይታወቃል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.