Fana: At a Speed of Life!

የባህረ ሰላጤው ሃገራት ኳታር ላይ የጣሉት ማዕቀብ እንዲያበቃ የስምምነት ሰነድ ፈረሙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህረ ሰላጤው ሃገራት ኳታር ላይ የጣሉት ማዕቀብ እንዲያበቃ የዓረብ ሃገራት የትብብር መድረክ ላይ የስምምነት ሰነድ መፈረማቸውን አስታወቁ፡፡

ለሦስት ዓመታት የቀጠለው ማዕቀብ እንዲነሳ ስምምነት የፈረሙት በሳዑዲ ዓረቢያ የዓረብ ሃገራት የትብብር መድረክ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ነው ተብሏል፡፡

በስምምነቱ ላይ የኳታሩ ኤሚር ታሚም ቢን ሃሚድ አልታኒ ተገኝተዋል፡፡

የኳታሩ ኤሚርም ሳዑዲ መግባታቸውን ተከትሎ በሳዑዲው ልዑል ሞሃመድ ቢን ሳልማን ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

ሳዑዲ ዓረቢያ፣ የተባበሩት ኢሚሬትስ፣ ኩዌት እና ግብጽ፥ ኳታር ሽብርተኞችን በመደገፍና መረጋጋት እንዳይኖር ለተቃዋሚዎች ድጋፍ ታደርጋለች በሚል ነበር ማዕቀብ ጥለውባት የቆዩት፡፡

የማዕቀቡ መነሳት ተከትሎም የኳታርን ጨምሮ የእስያ ኢኮኖሚ መነቃቃት መሳየቱ ተገልጿል፡፡

 

ምንጭ፡-አልጀዚራ

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.