Fana: At a Speed of Life!

የባህር ዳሩ ነዋሪ ጓደኛው ባበረከተለት የሎተሪ ዕጣ የ1 ሚሊየን ብር ዕድለኛ ሆኗል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የባህር ዳር ከተማ ነዋሪ የሆነው ወጣት ከጓደኛው በተበረከቱለት ሁለት የሎተሪ ዕጣዎች የ1 ሚሊየን ብር ዕድለኛ ሆኗል።

በልብስ ንግድ የሚተዳደረው ወጣት አያሌው ጥላሁን፥ አንድ ቀን ምሽት የቅርብ ጓደኛው ሙሉ የልዩ ሎተሪ በ40 ብር ገዝቶ ሁለቱን እንዳበረከተለት ተናግሯል።

ወጣቱ በተበረከቱለት የሎተሪ ዕጣዎች በ4ኛ ዕጣ የ1 ሚሊየን ብር ዕድለኛ መሆኑን ከብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ባልታሰበ ስጦታ የደረሰውን ገንዘብም የንግድ ስራውን ለማስፋፋት እንደሚያውለው ተናግሯል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.