Fana: At a Speed of Life!

የባሌን የቱሪዝም መስህብነት ያስተዋወቀ የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባሌን የቱሪዝም መስህብ ማስተዋወቅን ዓላማው ያደረገ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በባሌ ሮቤ ተካሄደ።

የጎዳና ላይ ሩጫው ተዋቂው የባሌዎች አባባልና የሙዚቃ ርዕስ በሆነውና ‘መንገዶች ሁሉ ወደ ባሌ’ የሚል ትርጉም ያለው አባባል “ባሌሆ ከራን” የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።

በኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽንና በሳዲያ መልቲ ሚዲያ ትብብር በተዘጋጀው በዚሁ የጎዳና ላይ ሩጫ የ2014 ‘ሚስ ቱሪዝም ኦሮሚያ’ የቁንጅና ውድድር አሸናፊ የሆነችው ሃሊማ አብዱልሸኩር ተገኝታ የውድድሩ ድምቀት ሆናለች።

ውድድሩን ያስጀመሩት የሮቤ ከተማ ከንቲባ አቶ ገዛኸኝ ደጀኔ እንዳሉት በበርካታ የቱሪዝም መስህብነቷ በሚትታወቀው ባሌ መሰል የጎዳና ላይ ሩጫ ሲካሄድ የባሌን የቱሪዝም ማስህብ ከማስተዋወቅ ባለፈ የአካባቢውን የንግድ እንቅስቃሴን ያነቃቃል።

የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ተወካይ አቶ ፍጹም ካሳሁን በበኩላቸው ኮሚሽኑ የክልሉን የቱሪዝም መስህቦች በማስተዋወቅ የአገሪቷን የዘርፉን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ይሰራል ብለዋል።

በዞኑ ለ3ኛ ጊዜ የተዘጋጀው ታላቅ የጎዳና ላይ ሩጫም የዚሁ ጥረት ማሳያ ነው ብለዋል አቶ ፍጹም።

በሮቤ ጄኔራል ዋቆ ጉቱ አዳባባይ መነሻና መዳረሻ በሆነው በዚሁ የጎዳና ላይ ሩጫ አትሌቶችን ጨምሮ ወደ 3 ሺህ ሰዎች ተሳትፈውበታል ብሏል የኢዜአ ዘገባ።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.