Fana: At a Speed of Life!

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የበረሃ አንበጣን ለመከላከል የሚረዳ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰራ መድሐኒት መርጫ ሰራ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት የበረሃ አንበጣን ለመከላከል የሚረዳ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰራ መድሐኒት መርጫ መስራቱን አስታወቀ፡፡

መድሃኒት መርጫው በኤሌክትሪካል እና ኮምፒውተር ምህንድስና ትምህርት ክፍል መምህራኖች የተሰራ ነው ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ የተከሰተውን የበረሃ አንበጣ ወረርሽኝ ለመከላከል እንደሚያስችል የጠቀሰው ኢንስቲቲዩቱ ለአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ማስረከቡንም ነው የገለጸው፡፡

ከዚህ ቀደም የነበረው መርጫ እስከ አምስት ሜትር የሚረጭ ሲሆን አሁን የተሰራው እስከ 15 ሜትር ከፍታ መርጨት እንደሚችል ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.