Fana: At a Speed of Life!

የቤት ስራውን ባለማከናወኑ ምክንያት አባት ልጁ ላይ የወሰደው እርምጃ ብዙዎቹን አስቆጥቷል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቤት ስራውን ባለማከናወኑ ምክኒያት አንድ ቻይናዊ አባት የ10 ዓመት ልጁ ላይ  የወሰደው እርምጃ ብዙዎቹን አስቆጥቷል።

ይህ ቻይናዊ አባት የ10 ዓመት ልጁ ቤት ስራውን መስራት አልቻለም በሚል ምክንያት በሻንጋይ የባቡር ጣቢያ ውስጥ እንዲለምን መጠየቁ ተሰምቷል።

በመቀጠልም ቻይናዊው አባት ልጁን አከባቢው ወደ ሚገኘው ባቡር ጣቢያ አድርሶት ሲመለስ ታዳጊው የተወሰነበት ቅጣት  በመቀበል ትንሽ ሳህን በመያዝ ከሰዎች ምግብ ይለምናል።

ይህን የተመለከተ አንድ ግለሰብ ለፖሊስ ደውሏል፤ ፖሊስ ሲድርስም ታዳጊው ሳህን በመያዝ ተንበርክኮ ሲለምን አግኝቶታል።

ስለሁኔታው ሲጠየቅም የቤት ስራዬን አልጨረስኩም ለዛም ነው አባቴ እንደ ቅጣት አድርጎ ተንበርክኬ ምግብ እንድለምን የነገረኝ በማለት ምላሽ ሰቷል።

የታዳጊው እናትም በውሳኔው እንዳልተሰማማቸ እና በተደጋጋሚ ቤት ስራው ባለመስራቱ ምከንያት ይህን እንዳደረገ ገልጻለች።

በተጨማሪም ጠንክሮ ማማር ካልቻለ አስቸጋሪ ሕይወት እንደሚገጥመው ለማስተማር ነው በማለት ተናግራለች።

ይህ ከባድ ቅጣት በቻይና ውስጥ ያልተለመደ ሲሆን፥ ቅጣቱ በራስ የመተማመን ስሜትን እንደሚጎዳ ነው የተነገረው።

ግለሰቡ ላይም በመንግስት ምን አይነት እርምጃ እንደሚያስወስድ የተገለጸ ነገር እንደሌለም ታውቋል።

ምንጭ፦ ኦዲቲ ሴንተራል

በፌቨን ቢሻው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.