Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለአገር መከላከያ ሰራዊት 284 የእርድ እንስሳትና 40 ኩንታል ስንቅ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለአገር መከላከያ ሰራዊት 284 የእርድ እንስሳት እና 40 ኩንታል ስንቅ ድጋፍ አደረገ።

ከክልሉ ከተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች ህብረተሰቡ ያዋጣውን ድጋፍ የአገር ሽማግሌዎችና የማህበረሰብ ተወካዮች ለአገር መከላከያ ሰራዊት አስረክበዋል።

በዛሬው ዕለት የተደረገው ድጋፍ 243 በግና ፍየሎች፣ 41 ሰንጋ እና 40 ኩንታል ደረቅ ስንቅ ሲሆን ክልሉ ከዚህ ቀደም 20 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ተመሳሳይ ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።

በተመሳሳይ በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተስፋ ለኢትዮጵያ በተባለ ድርጅት አማካኝነት 52 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ አድርገዋል።

በኒውዮርክ፣ ኒውጀርሲ እና ሌሎችም አካባቢዎች የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ናቸው የገንዘብ ድጋፋን ያደረጉት።

ድጋፎቹን የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ መረከባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.