Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ50 ሚሊየን ብር ወጪ የተገዙ ትራክተሮችን ለአርሶ አደሮች አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ በ50 ሚሊየን ብር ወጪ የተገዙ የእርሻ ትራክተሮችን ለአርሶ አደሮች አስረከበ፡፡
የግብርና ሜካናይዜሽን ቴክኖሎጂን በመጠቀም የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑንም ቢሮ አስታውቋል፡፡
የእርሻ ትራክተሮችን ለአርሶ አደሮች ያስረከቡት የክልሉ ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ምክትል ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ብርሃኑ ኢትቻ፥ ቢሮው 50 ሚሊየን ብር በሆነ ወጪ የተገዙ 24 የእርሻ ትራክተሮችን ለአርሶ አደሮች ማስረከቡን ተናግረዋል፡፡
ክልሉ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን በቀዳሚነት ወደ ስራ ገብቷል ያሉት ደግሞ÷ በክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ካሚል ሀሚድ ናቸው፡፡
የግብርና ሜካናይዜሽን ቴክኖሎጂን ማስፋፋት ምርትና ምርታማነትን ከመጨመር ባለፈ የሰውና የእንስሳት ጉልበት ለመቆጠብ የሚያበረክተው አስተዋፀኦ የጎላ መሆኑን ትራክተሮቹን የተረከቡት አርሶ አደሮች መግለጻቸውን የክልሉ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.