Fana: At a Speed of Life!

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ወቅታዊ  መግለጫ  ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ወቅታዊ መግለጫ ሰጥቷል።
መግለጫውን የሰጡት የቦርዱ የኮሙኒኬሽን ሃላፊ ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ ናቸው።
በዚህም መግለጫ ቁሳቁስ እሸጋ እና ስርጭት በሚመለከት በኦሮሚያ 118 ፣በድሬዳዋ 47 ፣በአፋር 25፣ በቤንሻንጉል 7 ጋምቤላ 14 በሚሆኑ የምርጫ ክልሎች ቁሳቁስ ታሽገው ዛሬን ጨምሮ ስርጭት መጀመሩን ሃላፊዋ ገልጸዋል።
አማራ ክልል 1/3ኛው የተሰራጨ ሲሆን÷በቀጣይ ቀናት እንደሚጠናቀቅም ነው የተናገሩት።
በአዲስ አባባ በመጨረሻዎቹ ቀናት ስርጭቱ እንደሚደረግ ወ/ሪት ሶሊያና ገልጸዋል።
ቀደም ሲል የነበሩት እና ለመራጮች ምዝገባን ብቻ ታሳቢ በማድረግ የተዘጁ ቦታዎች ለቀጣይ ስራ ምቹ ስለማይሆኑ ፣ ለምርጫ እና ለድምጽ ቆጠራ የሚሆኑ ምቹ እና ሰፊ ቦታዎችን እንዲያዘጋጁ ቦርዱ ጥያቆ ማቅረቡን ገልጸዋል።
ለዚህም ተግባራዊነት እየተሰራ ነው ሲሉ ሃላፊዋ በሰጡት መግለጫ ጠቅሰዋል።
በክልሎች እና በገጠር ከተሞች የምርጫ አሰጣጥን የተመለከተ የግንዛቤ ትምህርቶች በመከናወን ላይ እንደሚገኝ እና አካል ጉዳተኞችን ያማከሉ ስራዎችን ቦርዱ እየሰራ እንደሚገኝ አንስተዋል።
ከዛሬ ጀምሮ በማህበራዊ ሚዲያ አልፎ አልፎ የሚታይ ቅስቀሳዎች ተገቢነት ስለሌላቸው ሊቆሙ እንደሚገባ ገልጸዋል ።
በፍሬህይወት ሰፊውና አፈወርቅ እያዩ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.