Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ከነገ ጀምሮ 1ኛ ጉባኤውን ያካሂዳል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ከነገ ጀምሮ አንደኛ ጉባኤውን በሀዋሳ ከተማ ያካሂደል፡፡
በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ የተመራ የልዑካን ቡድን ሀዋሳ ገብቷል፡፡
የልዑካን ቡድኑ አባላት በብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ 1ኛ ጉባኤ ላይ ለመገኘት ነው ሀዋሳ የገቡት፡፡
የልዑካን ቡድኑ አባላት ሀዋሳ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ÷ የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መሰረት መስቀሌ፣ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ እና ሌሎች አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ እንደገለጹት÷ የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ 1ኛ ጉባኤውን በሀዋሳ ከተማ ማካሄዱ ለከተማዋና ለሲዳማ ሕዝብ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.