Fana: At a Speed of Life!

የብልፅግና ፖርቲ አመራሮች በዱከም ኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞንን እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የብልፅግና ፖርቲ አመራሮች በዱከም ከተማ የሚገኘውን ኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞንን በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ።

በጉብኝታቸውም የኢንዱስትሪ ዞኑን የስራ እንቅሰቃሴ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ የአመራር ስልጠና ከጥር 16 ጀምሮ በአዳማ ከተማ ስልጠና ላይ የሚገኙ ሲሆን፥ ስልጠናውም እስከ የካቲት 2 2012 ዓ.ም ድረስ ቀጥሎ የሚካሄድ ይሆናል።

ስልጠናው ፓርቲው ከኢህአዴግ ወደ ብልፅግና ሃገራዊ ውህድ ፓርቲ ከተሸጋገረ በኋላ በየደረጃው ለሚገኙ ከፍተኛ አመራሮች በብልፅግና ፓርቲ ምንነትና አስተሳሰብ ዙሪያ የተዘጋጀ ነው ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም በተጀመረው ሃገራዊ ለውጥና ከለውጡ ጋር ተያይዞ በተወሰዱ እርምጃዎች፣ በተገኙ ስኬቶችና የቀጣይ ስጋቶች ላይ አመራሩ የተግባር አንድነት እንዲኖረው ለማድረግ ታልሞ የተዘጋጀ መሆኑንም ተገልጿል።

በተጨማሪም ለሃገሪቱ ህዝቦች የለውጥ ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል አቅም ለመገንባትና ለቀጣይ ተልዕኮ ለማዘጋጀት ታስቦ የተዘጋጀ ነው መባሉም ይታወሳል።

 

በሀይለኢየሱስ መኮንን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.