Fana: At a Speed of Life!

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሃሰተኛ መረጃዎችን የሚያሰራጩ የማህበራዊ ሚድያ አንቂዎች ከህገወጥ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሃሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት ህብረተሰቡን ለማደናገር የሞከሩ የማህበራዊ ሚድያ አንቂዎች ከህገወጥ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ አሳሰበ፡፡

ሰሞኑን ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብታቸውን ያላግባብ ተጠቅመው አገልግሎቱን በተመለከተ ሃሰተኛ መረጃዎችን በማህበራዊ ትስስር ገጾቻቸው በማሰራጨት ህብረተሰቡን ለማደናገር ሲሞክሩ የነበሩ አንዳንድ የማህበራዊ ሚድያ አንቂዎች ከህገወጥ ድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ ተቋሙ አሳስቧል፡፡

አገልገሎት መሥሪያ ቤቱ ከዚህ በኋላ የሀሰት መረጃዎችንና አሉባልታዎችን  በማህበራዊ ትስስር ገጾች በማሰራጨት  የሀገርን ብሄራዊ ጥቅምና ህልውና ለመጉዳት እንዲሁም የህዝብን ሰላምና  ደህንነት ስጋት  ላይ ለመጣል  የሚንቀሳቀሱ  አካላት ላይ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ማስረጃዎችን በማጠናቀር በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ እንደሚያደርግ ማስታወቁን ኢዜአ ዘግቧል።

ብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት  በሀገር ላይ የሚቃጡ  የፀጥታና የደህንነት  ስጋቶችን በማስቀረት  ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን  ከማንኛውም ጊዜ በላይ ከሁሉም የጸጥታና የደህንነት ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ እንደሚገኝ መግለጫው አመልክቷል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.