የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ስልጠና አላማውን ያሳካ ነው-የስልጠናው አስተባባሪዎችና አሰልጣኞች
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ስልጠና አላማውን ያሳካ መሆኑን የስልጠናው አስተባባሪዎችና አሰልጣኞች ተናገሩ ።
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ሰልጣኞችን እያሰለጠኑ የሚገኙ ባለሙያዎች÷ ስልጠናው በጎ ፈቃደኞችን በአስተሳሰብ ፣ በአመለካከትና በክህሎት የለወጠ ነው ብለዋል ።
ሰልጣኝ ወጣቶች ስለ ሀገራቸው ዘላቂ ሰላም ፣ ልማት ፣ ብዝሃነት ፣ ሀገራዊ አንድነትና ኢትዮጵያዊነት በቂ ግንዛቤ እንዲያገኙ ተደርጓል ብለዋል ።
በስልጠናው ወጣቶች ራሳቸውን ፈልገው እንዲያገኙ፣ የነገ የህይወት መስመራቸውን እንዲለዩ እና ወገን ማገልገል ክብር መሆኑን እንዲረዱ ሰፊ ስራ ተሰርቷልም ነው ያሉት ።
በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በቀጣይ የበጎ ፈቃድ ተግባር ለመስጠት በሚሰማሩባቸው አካባቢዎች የተዋጣለት የበጎ ተግባር ስራ መስራት የሚያስችላቸውን ስንቅ በስልጠናው ማግኘታቸውን ገልፀዋል ።
የሰላም ሚኒስቴር የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራምን በሀገር ደረጃ ቀርፆ መጀመሩ የተረጋጋችና ሰላሟ የተረጋገጠ ሀገር ለመገንባት የጀመረውን መንገድ ማሳያ መሆኑን የስልጠናው አስተባባሪዎችና አሰልጣኞች መናገራቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!