Fana: At a Speed of Life!

የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀንን ለማክበር ዝግጅት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 16ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀንን በድምቀት ለማክበር አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ገለጹ።
 
ከንቲባው በድሬዳዋ አስተዳደር አዘጋጅነት “ወንድማማችነት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በዓል መሪ ቃል ዘንድሮ ለ16ኛ ጊዜ የሚከበረው የኢትዮጵያ የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
 
የዘንድሮው የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን የትንሿ ኢትዮጵያ መገለጫ በሆነቸው የፍቅር ፣ የሠላምና የመቻቻል ከተማ በሆነቸው ድሬዳዋ ያለምንም የፀጥታ ስጋት ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁንና እንግዶችን ለመቀበል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።
 
በዓሉ የኮቪድ 19 መከላከያ ደንቦችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንደሚከበርና በዚሁ ጋር በተያያዘም በቂ የህክምና ተቌማትና ባለሙያዎች መዘጋታቸውን ያነሱት አቶ ከዲር በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር በሠላም እንዲጠናቀቅም የፀጥታ ኃይሉ በቂ ዝግጅት እንዳደረገም አስታወቀዋል።
 
የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በኢትዮጵያውያን መካከል ያለውን ወንድማማችነት በሚያጐላ መልኩ ለሀገር ሉዓላዊነት መከበር የህይወት መሰዋትነት እየከፈለ ለሚገኘው መከላከያ ሠራዊት የድሞ ልገሳ እንደሚደረግና ድሬዳዋ የሚገኘው የሀዳሴ ግድብ ዋንጫም ለቀጣይ ክልል የማስረከብ ስነ ስርአት እንደሚካሄድ ተገልጿል።
 
የዘንድሮው 16ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል ሉላዊነቷ የተረጋገጠ ነፃ ሀገር መሆኗን በማረጋገጥ የህልውና ዘመቻ እየተደረገ ባለበት ወቅት በድል ታጅቦ የሚበበር በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል ያሉት አቶ ከዲር ጁሃር፥ ምዕራባውያን ሀገሪት በትርምስ ውስጥ ናት እያሉ የሚነዙት ፕሮፖጋንዳ መሰረተ ቢስ መሆኑን በተግባር ለማሳየት የሚያስችል ነው ብለዋል።
 
በተሾመ ኃይሉ
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.