Fana: At a Speed of Life!

የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በሐረሪ ክልል ተከበረ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 16ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በሐረሪ ክልል ምክር ቤት በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች ተከብሯል።
 
በዓሉ ”ወንድማማችነት ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል ነው የተከበረው፡፡
 
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦድሪን በድሪ በዓሉ እውነተኛ የፌደራሊዝም ስርዓት እየተተገበረ ባለበት ማግስት መከበሩ ለየት እንደሚያደርገው አውስተዋል፡፡
 
ብሄሮች ብሄረሰቦች አንድ ሆነው ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት መከበር መትጋት አለባቸው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ÷ በሐረሪ ክልል በታሪኩ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የመከላከያ ሠራዊትን የሚቀላቀለው ወጣት ቁጥር እያደገ መምጣቱን ጠቁመዋል፡፡
የሐረሪ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ሱልጣን አብዱልሰላም በበኩላቸው፥ በዓሉ ወደ ሲኦል እሄዳለሁ ያለው አካል ወደ ሲኦል እየተሸኘ ባለበት ጊዜ መከበበሩ ለየት እንደሚያደርገው አንስተዋል።
 
ይህንን በጠነከረ ተጋድሎ እየፈፀመለሚገኘው ጀግናው የአገር መከላከያ ሠራዊት የሐረሪ ክልል ህዝብም የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
 
በእዮናዳብ አንዱዓለም
 
 
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.