Fana: At a Speed of Life!

የብረታ ብረት ምርትን በሚፈለገው መጠን ለማምረት ጥሬ እቃው በሀገር ውስጥ ሊተካ እንደሚገባ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብረታ ብረት ምርትን በሚፈለገው መጠን እና ብዛት ለማምረት የምርት ጥሬ እቃው በሀገር ውስጥ ሊተካ እንደሚገባ ተገለጸ።
የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስቴር ከብረታ ብረት አምራች ኩባንያዎች እና የፋብሪካ ባለቤቶች ጋር እየተወያየ ነው።
የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስትር ኢ/ር ታከለ ኡማ፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ለሊሴ ነሚ እና ሚኒስትር ዴኤታዎች እንዲሁም የዘርፉ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ከአምራቾቹ ጋር እየተወያዩ ነው፡፡
በውይይቱ የምርት ግብዓት እና ጥሬ እቃ ከውጭ ስለሚገባ በምንዛሬ እና በፋይናንስ አቅርቦት ችግር በመኖሩ አምራቾች በሙሉ አቅም እና በተገቢው መጠን እንዳያመርቱ ማድረጉ ተነስቷል።
ለዚህም የምርት ጥሬ እቃውን በሀገር ውስጥ በመተካት ምርቱን በጥሩ አቅም እና ጥራት ለማምረት መስራት እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡
በሀገር ውስጥ በተለያዩ የመንግስት ተቋማት ተከማችቶ የተቀመጠ ሃብትን አውጥቶ አምራቹ ሊጠቀምበትና ወደ ጥቅም ሊቀየር እንደሚገባ አምራቾች አንስተዋል።
በዘርፉ በቂ እና ብቁ የሰው ሃይል ማፍራት እንደሚገባ የተገለፀ ሲሆን÷ በሙያው የረዥም ዓመት ልምድ ያላቸውን የውጭ ሀገራት ዜጎችም ተገቢውን ሙያዊ አገልግሎት እንዲሰጡ እና ሙያቸውን እንዲያካፍሉ ሊበረታቱ እንደሚገባም ተጠቁሟል።

በፍሬህይወት ሰፊው

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.