Fana: At a Speed of Life!

የብቃት ማረጋገጫ መስፈርቶች ከ52 ወደ 10 ዝቅ እንዲሉ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቅድመ ንግድ ስራ ፍቃድ የብቃት ማረጋገጫ መደብ መስፈርቶች ከ52 ወደ 10 ዝቅ እንዲሉ ማድረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ በተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መሰረት የንግዱን ዘርፍ ቀላል፣ ግልፅና ተደራሽ ለማድረግ በቅድመ ንግድ ስራ ፍቃድ የሚጠየቀውን የብቃት ማረጋገጫ መደብ መስፈርትን ከልሷል፡፡
የንግድ ሥራ ፈቃድ ለማውጣት ብቃት ማረጋገጫ እንደ ቅድመ መስፈርት ይጠቀምባቸው የነበሩ 52 መደቦችን በመከለስ ወደ 10 ዝቅ እንዲሉ ተደርጓል ነው የተባለው፡፡
የሥጋና የስጋ ውጤቶች ማቀነባበርና መጠበቅ፣ የእንስሳት መኖና መሠረታዊ ኬሚካሎችን ማምረት፣ ለሰው አገልግሎት የሚውሉ የህክምና መድኃኒትና ኬሚካሎች ማምረት የንግድ ስራ ፈቃድ መስጫ መደቦች እንደሆኑ ተጠቅሷል፡፡
በተጨማሪም የእጽዋት ዘር እና የምግብ ምርቶች እንዲሁም ለግብርና አገልግሎት የሚውሉ ኬሚካሎች አስመጪ፣ የሰው መድሃኒትና የህክምና መገልገያዎችና መሳሪያዎች አስመጪነት፣ የእንስሳት መድሃኒት፤ የእንስሳት ህክምና ሥራዎች የንግድ ሥራ ፈቃድ መስጫ መደቦች መሆናቸውን ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
 
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.