Fana: At a Speed of Life!

የብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ  የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በልዩልዩ ኃላፊነትና በመንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ የበላይ ጠባቂነት ያገለገሉት የብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፅሟል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ እና የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የበላይ ጠባቂ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በትናትናው ዕለት ማረፋቸው የሚታወስ ነው፡፡

የቀብር ስነ ስርዓታቸው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የቤተ እምነት ተወካዮች እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት ተፈጽሟል፡፡

የብፁዕ  አቡነ ጢሞቴዎስ  ከአባታቸው ባላምባራስ ተስፋ ተክሉ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ታህሣ ኃይሉ በ1930 ዓ.ም ግንቦት ወር በትግራይ ክልል ብዘት ወረዳ የተወለዱት ብፁዕነታቸው÷ በተወለዱ በ83 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅትን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.