Fana: At a Speed of Life!

የተሃድሶ ስልጠና የተሰጣቸው የትግራይ ክልል ተወላጅ ፖሊስ አባላት በክልሉ ስምሪት እንደተሰጣቸው የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 9 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአጭር ጊዜ የተሃድሶ ስልጠና የተሰጣቸው የትግራይ ክልል ተወላጅ ፖሊስ አባላት በትግራይ ክልል ህዝብን እንዲያገለግሉ ስምሪት መስጠቱን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
ሕግ ማስከበር ዘመቻውን ተከትሎ በክልሉ ሰላምና መረጋት እንዲሰፍን፣ የክልሉን ጸጥታ ተቋማት ለማደራጀትና ቀሪ የጁንታ አመራሮችን አድኖ ለፍርድ ለማቅረብ እየሰራ መሆኑን ኮሚሽኑ ለኢዜአ በላከው መግለጫ አስታውቋል።
በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ሰላምና ጸጥታን ለማስፈንና ወንጀለኞችን የማደን ተልዕኮ በአገር መከላከያ ሰራዊትና በፌዴራል ፖሊስ የሕይወት መስዋዕትነት በተቀናጀ መንገድ በብቃት እየተወጡ መሆኑንም በመግለጫው አመልክቷል።
በዚህም ህዝቡን በሰላምና በፍትህ ለማርካት የክልሉ ተወላጅ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ተልዕኳቸውን በብቃት እንዲወጡ የተሃድሶ ስልጠና በመስጠት ወደ ክልሉ ስምሪት እንደተሰጣቸው ኮሚሽኑ ጠቁሟል።
በአፍ መፍቻ ቋንቋ ተናጋሪ ፖሊስ አባላትን አሰልጥኖ ወደ ክልሉ ማሰማራቱ ህብረተሰቡ ያጋጠሙትን ችግሮች በፍጥነት ለመቅረፍና የተበታተነውን የጥፋት ቡድን ለማጽዳት ስምሪቱ ወቅቱን የጠበቀ ነው ብሏል።
በጁንታው የሀሰት ፕሮፓጋንዳ የተጎዳ ህዝብ ወደቀደመ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅሰቃሴው በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲመለስ የፖሊስ አባላቱ ግዳጃቸውን በጥንቃቄና ትኩረት በተሞላበት አግባብ እንዲወጡ ሃላፊነት እንደተጣለባቸው ኮሚሽኑ ገልጿል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.